የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ

By Melaku Gedif

May 04, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ልዩ መልዕክተኛ ጋርመወያየታቸውን አስታወቁ።

በዚህ ወቅትም ሱዳን በልጆቿ ጥበብ እና በሳል ውይይት በአጭር ጊዜ ውስጥ አሁን ካለችበት ሁኔታ እንደምትወጣ ኢትዮጵያ ሙሉ እምነቷ መሆኑን ገልጸዋል።

የሱዳን ተፋላሚ ኃያሎችም ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።