Fana: At a Speed of Life!

የዐርበኞች የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ መድፍ ይተኮሳል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ ሚያዚያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም የሚከበረውን የኢትዮጵያ ዐርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ በመከላከያ ሚኒስቴር የስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት አስታወቀ።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ለአዲስ አበባ ፖሊስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ሚያዚያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.