Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዐርበኞች ቀን (የድል በዓል) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዐርበኞች ቀን (የድል በዓል) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
 
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፦
 
እንኳን ለዐርበኞች ቀን(የድል በዓል) አደረሳችሁ
 
ኢትዮጵያ የነጻነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ያላት ሀገር ነች። ነጻነታቸውን በምንም ነገር ለመቀየር ፈቃደኛ ያልሆኑት እናቶቻችን እና አባቶቻችን ለነጻነት ሲሉ ዋጋ ከፍለዋል።
 
እናቶቻችን እና አባቶቻችን ሕይወት ከፍለው ያቆዩልን ነጻነት ብቻቸውን አይቆምም። በሌሎች ነጻነቶች መደገፍ አለበት። ሀብት፣ ኅብረትና አገልጋይነት ሊደግፉት ይገባል።
 
በኢኮኖሚው ዘርፍ በርትተን ሀገራዊ ሀብት ካልፈጠርንና ከርዳታ ካልተላቀቅን ነጻነት ብቻውን ሩቅ አይወስደንም። ኩሩ ድኻ ያደርገናል እንጂ። ኅብረት ፈጥረን መለያየትንና መከፋፈልን ካላሸነፍን ነጻነት ብቻዉን ኃይል አይሆነንም። በኅብረት ያገኘነው ነጻነት በመለያየት በፈቃዳችን እናጣዋለንና።
 
ሀገርንና ሕዝብን በቅንነትና በትጋትና በንጽሕና ለማገልገል ካልወሰንን ነጻነት ብቻውን ዕድገት አያመጣም። ሙስና፣ ኋላ ቀር አሠራርና ስንፍና ወደኋላ ይጎትቱናልና።
 
የድል ቀናችንን ስናከብር ከዐርበኞቻችን ድል በኋላ ያስመዘገብናቸውን ድሎች በመቁጠር መሆን አለበት። ድል የማይወልድ ድል ድል አይባልም።
 
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
 
 
ሚያዚያ 27፣ 2015 ዓ.ም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.