የሀገር ውስጥ ዜና

2ኛው የኦሮሚያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ካውንስል ስብሰባ እየተካሄደ ነው

By Amele Demsew

May 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው የኦሮሚያ ክልል ግብርና ትራንስፎርሜሽን ካውንስል ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ እና የፌዴራል የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኦሮሚያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ካውንስል ግብርናን በእውቀት እና በምርምር በመደገፍ ውጤታማ ማድረግን አላማ አድርጎ የተመሰረተ ነው፡፡