ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያላትን ልምድ ለአፍሪካ ሀገራት እንድታካፍል ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያላትን ልምድ እና የሰው ሃይል ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንድታካፍል የአፍሪካ ሲዲሲ ጠየቀ።
የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) አዲስ ከተሾሙት የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዢን ካሴያን ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅት የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዢን ካሴያን (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያላትን ልምድ እና የሰው ሀይል ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንድታካፍል ጠይቀዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሲወስድ የነበራቸውን እርምጃዎች አድንቀዋል።
በተለይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት ህይወት አድን የሆኑ የጤና ቁሳቁሶችን በማድረስ በኩል ላበረከተው እስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ለግሰዋል።
የጤና ሚኒስትርሊያ ታደስ (ዶ/) ር በበኩላቸው÷ ጤና ሚኒስቴር ከአፍሪካ ሲዲሲ ጋር በተለያዩ የህብረተሰብ ጤና ጉዳዮች ላይ በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይ ክትባትን ተደራሽ በማድረግና ለማምረት በሚደረገዉ ጥረት እንዲሁም የጤና ስርአት በማጠናከር በኩል ያለው ትብብር ጠንካራ መሆኑም አስታውቀዋል።
በቀጣይም ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸው÷ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሰው ሀብቷን ለማልማት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ማፍሰሷን አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ ልምዷን ከማካፈል ባለፈ ያፈራችውን የጤና ዘርፍ የሰው ሀብት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ ናት ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!