የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 9 ወራት በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው – አቶ ርስቱ ይርዳ

By Amele Demsew

May 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተገኘው አንጻራዊ ሰላም በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ገለጹ፡፡

የደቡብ ክልል መንግስት የዘጠኝ ወራት የዕቅ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሔደ ነው ፡፡

አቶ ርስቱ ÷በክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተገኘው አንጻራዊ ሰላም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሰላምን ማጽናት እንደሚገባ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ባለፉት 9 ወራት የታዩ መልካም ልምዶችን በማስቀጠል እና የታዩ የአፈጻጸም ውስንነቶችን በቀሪ ወራት ፈጥኖ በማረም የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል፡፡

በክልሉ እየታየ ያለው የዝናብ ስርጭት ለበልግ ስራ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው ያሉት አቶ ርስቱ÷በዚህም ከ1 ሚሊየን ሔክታር በላይ መሬት በበልግ ወቅት የማልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አንስተዋል።