የሀገር ውስጥ ዜና

የከተማ አስተዳደሩ የ9 ወራት ስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሄደ  

By Amele Demsew

May 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ፡፡

በግምገማ መድረኩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ በመድረኩ በተሰሩ ዋና ዋና ስራዎች የተሳኩ ግቦችን በጥንካሬ ይዞ ለመቀጠል፣ ክፍተቶችን ደግሞ ለመሙላት እንዲሁም መታረም ያለባቸው ድክመቶች በመለየት ለማስተካከል መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡

እንደ በጎ የሚወሰዱና መስፋት ያለባቸው መልካም ተሞክሮዎች እና ጥንካሬዎች በማስፋት ለከተማዋ እና ለህዝቡ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

ከተማዋን እና ህዝቦቿን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት ከዚህ በላይ የተቀናጀ፣ የሚናበብ እና የተደራጀ የአመራር ቁመናን ለማጠናከርም በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡