Fana: At a Speed of Life!

ከ8 ሺህ በላይ በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች ለስራ ወደ ውጭ ሀገራት ተጉዘዋል-ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት ሳምንታት ከ8 ሺህ በላይ በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች ለስራ ወደ ውጭ ሀገራት መጓዛቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

ባለፉት አጭር ጊዜያት የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ዘርፉን የማዘመን ሂደት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ጥቅም ላይ የማዋል ሥራ መጀመሩንም ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ሂደቱ በተሻለ ደረጃ የዜጎችን ተጠቃሚነትና ደህንነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

በዚህ ረገድ ተሳትፎ ላደረጉ አጋዥ አካላት ምስጋና ያቀረቡት ሚኒስትሯ ሚኒስቴሩ በቀጣይ ለሚኖረው የላቀ የስኬት ጉዞ ያላሰለሰ ጥረቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.