የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያን አንደኛዋ ባለትልቅ ኢኮኖሚ ማድረግ አይሳነንም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

By ዮሐንስ ደርበው

May 06, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን አንደኛዋ ባለ ትልቅ ኢኮኖሚ ማድረግ ይገባናል፤ ይህም አይሳነንም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

የበለጸገች እና ለሁሉም ምቹ የሆነች ሀገርን ለመገንባት ኢንዱስትሪዎቻችንን በማሳደግ፣ ዐቅምን በመፍጠር እንዲሁም ፈጠራ በታከለበት መንገድ ፈተናዎችን በማለፍ ኢትዮጵያን አንደኛዋ ባለ ትልቅ ኢኮኖሚ ማድረግ ይገባናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ይህን ማሳካትም አይሳነንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡