Fana: At a Speed of Life!

200 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተቋቋመው የፀረ ሙስና ኮሚቴ 200 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማ አስተዳደሩ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በተለያየ ደረጃ በቀረቡ በርካታ ጥቆማዎች ላይ ምርመራ በማድረግ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ገልጸዋል።

ኮሚቴው በእስከአሁኑ እንቅስቃሴው ከ90 በላይ የምርመራና የክስ መዝገቦችን ማደራጀቱንም ጠቁመዋል፡፡

ለሙስና ተጋጭ በሆኑ መሬት፣ ኮንስትራክሽን፣ የግዥ ስርዓት፣ የታክስ፣ የጤና፣ የትምህርት ዘርፎች ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና የተጋላጭነት መጠንን የሚቀንስ አሰራር እየተዘረጋ ነው ብለዋል፡፡

ጥቆማ የሚቀበል፣ መረጃ የሚያሰባስብ፣ ምርመራና ጥናት የሚያካሂድ ንዑስ ኮሚቴ ተቋቁሞ የልየታ ሥራ ማከናወኑንም ነው ኮሚሽነሩ ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

የፀረ ሙስና ኮሚቴው ጥቆማ የማሰባሰብ ሂደቱን እንደጀመረ የማህበረሰቡ ተሳትፎ አነስተኛ እንደነበር አስታውሰው÷ በተጠርጣሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተከትሎ የህብረተሰቡ የጥቆማ ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱን አንስተዋል።

ለአብነትም በአንድ ሳምንት ብቻ 500 ያህል ጥቆማዎች ለኮሚሽኑ የቀረቡ ሲሆን÷ ይህም ህብረተሰቡ ሙስናን የመታገል ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ያሳየ በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል ነው ያሉት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.