የሀገር ውስጥ ዜና

ከ”መደመር ትውልድ” መጽሐፍ 400 ሚልየን ብር ተሰበሰበ

By ዮሐንስ ደርበው

May 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ከ”መደመር ትውልድ” መፅሐፍ 400 ሚልየን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በሶማሌ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

አቶ ሙስጠፌ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ወጣቱ ትውልድ የማንበብ ባህሉን ማዳበር አለበት ብለዋል፡፡

ሕብረተሰቡም የመደመር ትውልድ መጽሐፍን በማንበብ ዕውቀትን መቅሰም ይኖርበታል ነው ያሉት፡፡

ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በክልሉ ትላልቅ ከተሞች ዘመናዊ የወጣት ማዕከላት ግንባታ ይውላል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ማዕከላቱም÷ የመጽሐፍ ማንበቢያ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የሲኒማ መመልከቻ ስፍራን የሚያትት መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን