Fana: At a Speed of Life!

በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ኢንቨስት ከሚያደርጉ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ኢንቨስት ከሚያደርጉ አምስት የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረሟል።
 
የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ በስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት÷ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ መሰማራታቸው የሀገሪቱን የጤና ሽፋን ያሳድጋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም በዘርፍ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት በኩል ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል ነው ያሉት።
 
ኩባንያዎቹ ወደ ስራ ሲገቡ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርቡ ሲሆን÷ ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድልን ይፈጥራሉ ተብሏል።
 
ኢንቨስትመንቶቹን የሚያስተናግደው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የተቋቋመ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.