Fana: At a Speed of Life!

የንግድ ተግባሩን ባስተጓጎሉ 25 ሺህ 68 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የንግድ ተግባሩን ባስተጓጎሉ 25 ሺህ 68 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በሰጡት መግለጫ በንግድ ተቋማቱ ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከማሸግ የደረሰ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።

በዚህም 13 ሺህ 350 ተቋማት ሲታሸጉ 404 የንግድ ተቋማት ደግሞ ፈቃዳቸው መታገዱን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም 890 የንግድ ፈቃድ መሰረዙን እና ለ10 ሺህዎቹ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንም አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም 420 ግለሰቦች ታስረዋልም ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የምርት አቅርቦትን ለማሻሻል እና ምርትን በሀገር ውስጥ ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በለይኩን ዓለም

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.