Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል የመንግስት ሰራተኞ የስራ ሰዓት ወደ መደበኛው መመለሱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሙቀቱ መጠን እየቀነሰ በመምጣቱ የመንግስት ሰራተኞ የስራ ሰዓት ከነገ ጀምሮ ወደ መደበኛ ሰዓት እንደሚመለስ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በለውጡ መሰረት ላለፉት ሶስት ወራት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ አምስት ስዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሰዓት እስከ ስድስት ተኩል እንዲሆን ተወስኗል።

እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከአስር ሰዓት እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል የነበረው ከዘጠኝ ስዓት እስከ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ወደ ቀድሞው እንዲመለስ ተደርጓል ነው የተባለው።

የክልሉ የመንግስት ሰራተኞችም ይህንን አውቀው በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ቢሮ በመግባት የተለመደውን ሥራቸውን እንዲያከናውኑ የክልሉ መንግስት አሳስቧል።

በጋምቤላ ክልል የመቀቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ከየካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የስራ ሰዓት ለውጥ ተደርጎ እንደነበር ከጋምቤላ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.