ኢትዮጵያና ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ የ106 ነጥብ 54 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (አይ ኤፍ ኤ ዲ) የ106 ነጥብ 54 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ሳራ ምባንጎ-ቡን ፈርመውታል።
ከድጋፉ የሚገኘው ገቢ በኢትዮጵያ ለአሳታፊ ግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም ትግበራ የሚውል ነው ተብሏል፡፡
ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ የ150 ሺህ አባወራዎችን ህይወት በዘላቂነት ለማሻሻል እና የአየር ንብረት ለውጦችን የመቋቋም አቅምን መገንባትም የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
በቤተልሔም መኳንንት