የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከማልታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

May 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማልታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢያን ቦርግን ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷የማልታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢያን ቦርግን ዛሬ አግኝቻቸዋለሁ ብለዋል።

በንግድ እና በኢንቨስትመንት ግንኙነት ላይ፣ በተለይም የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ በተጠናከረ መልኩ ከማልታ ጋር ስለምንሠራበት ሁኔታ ተወያይተናልም ነው ያሉት።