Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በኢትዮጵያ የህብረቱ አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ገለፁ፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፖ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ነገ የሚከበረውን 72ኛውን ”የአውሮፖ ቀን” አስመልክተው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው የህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባካሄዱት ስብሰባ የህብረቱ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያንና የህብረቱን አጋርነት ያረጋገጠ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ገልፀዋል።

ይህን ተከትሎ ህብረቱ ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ ቁልፍ አጋርነቷን በማጠናከር በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ለመስራት የተለያዩ ስምምነቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ለህብረቱ የረጅም ጊዜ እና ታሪካዊ ግንኙነት ያላት ሀገር መሆኗን ያነሱት አምባሳደሩ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የነበረውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የተደረገውን ጥረት ህብረቱ አድንቋል ብለዋል።

ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የነበሩ የሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ፕሮግራሞችን ህብረቱ ዳግም እንደሚያስጀምር በመጥቀስም በየደረጃው ካሉት የመንግስት አካላት ጋር የሚያደርገውን የፖለቲካ ውይይት እንደሚቀጥል አንስተዋል።

ህብረቱ የሽግግር ፍትሕን በተመለከተ የተጀመረውን ስራ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መመዘኛዎች እና ደንቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስድ እና  ህዝቦች በሰላማዊ መንገድ እንዲኖሩ የሚደረገውን ጥረት  እንደሚያግዝ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የሰብዓዊ አቅርቦቶች ተደራሽ እንዲሆኑ ህብረቱ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አምባሳደሩ በአውሮፓ ገበያ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላትንም  ጠቁመዋል።

ህብረቱ በተለይም በአውሮፖ ሃገራት የኢትዮጵያን ምርት ከቀረጥ ነፃ መላክን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ጠንካራ አጋር በመፍጠር ሲሰራ መቆየቱንም አውስተዋል።

በምንይችል አዘዘውባለፍት ጊዜያት ኢትዮጵያ ከህብረቱ ጋር በርካታ ስራዎችን ስትሰራ መቆየቷን እና አሁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

በተለይ በአውሮፖ ሃገራት የኢትዮጵያን ምርት ከቀረጥ ነፃ መላክን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ጠንካራ አጋር በመፍጠር ሲሰራ መቆየቱን  ነገር ግን ይህ በቂ አለመሆኑን አመላክተዋል።

በምን ይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.