ስፓርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር በሞዛምቢክ ይጫወታል

By Mikias Ayele

May 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ ጋር በሞዛምቢክ ሜዳ እንደሚጫወት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ 5ኛ የምድብ ጨዋታውን ሰኔ 13 ቀን የሚያደርግ ሲሆን ጨዋታውን በሞዛምቢክ ስታዲየም ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ለካፍ አሳውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ስታዲየሞች ላይ ለማከናወን ጥረት ቢያደርግም ባለመሳካቱ ምክንያት ሞዛምቢክ የዋሊያዎቹ ምርጫ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ቀደም ሲል በሞሮኮ ባደረጋቸው 3ኛ እና 4ኛ የምድብ ጨዋታዎች በጊኒ አቻው በደርሶ መልስ መሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡