የሀገር ውስጥ ዜና

ለገበታ ለትውልድ ፕሮጄክት የሚደረገው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው

By Mikias Ayele

May 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ13ኛው ዙር የገበታ ለትውልድ ፕሬጄክት ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትና ድርጅቶችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ኖርኒኮ 15 ሚሊየን ብር፣ ደርባ ሲሚንቶ፣ 10 ሚሊየን ብር እንዲሁም ድሬ ብረታብረት 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም የቻይና የምድር ባቡር ግሩፕ፣ የቻይና ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ዦንግሜይ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ሻንዶንግ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና ቱሉ ካፕ የወርቅ አምራች ኩባንያ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

እስካሁን ለገበታ ትውልድ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በአጠቃላይ 7 ቢሊየን 315 ሚሊየን 725 ሺህ 232 ብር ተሰብስቧል፡፡