Fana: At a Speed of Life!

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

ጉባኤውን በፀሎት የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጉባኤው የቤተክርስቲያኗን አብይ ተልዕኮ ለመፈፀም እንደመሳሪያ ሊያገለግሉ ይችላሉ ተብሎ ታምኖባቸው የተጀመሩ ወሳኝ ስራዎች በዝርዝር በማየት ውሳኔ የሚተላለፍበት ጉባኤ እንደሚሆን ተናግረዋል።

“በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖችንና የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናትን በፍጥነት ደርሰን የምናፅናናበትና የምንደግፍበትን ሁኔታ በጉባኤው እናያለን” ብለዋል።

ምሰሶ የቤትን ጣራ በቋሚነት እንደሚሸከመው ሁሉ ሰላምም በተመሳሳይ የሰዎችን መንፈሳዊ እና አካላዊ ህይወት ቀጥ አድርጋ የምትይዝ ናት ብለዋል ቅዱስነታቸው።

አያይዘውም አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ጠንክሮ የማስተማር የመምከርና የማስታረቅ ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በግጭት እየተሳተፋ ያሉ ወገኖች ግጭቱን አቁመው በሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ለመፍታት እንዲጥሩ አባታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በዙፋን ካሳሁን እና ቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.