የኢንዱስትሪ ምርቶች ጥራትና ተወዳዳሪነት ላይ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ምርቶች ጥራትና ተወዳዳሪነት ላይ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይት መድረኩ የንግድ እና ቀጣናዊ ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለው መኮንን ፣ የኢንዱስትር ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታን ጨምሮ የዘርፉ ምሁራን እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
አቶ እንዳለው መኮንን አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለገበያ ማቅረብ ቅድሚያ ትኩረትሊሰጡት የሚገባ ተግባር መሆኑን አንስተዋል፡፡
በተለይም በተኪ ምርቶች ላይ የሚሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ከጥራት አንጻር ዓለም አቀፍ ገበያው ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ሊገነዘቡ እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በኢትዮጵያ የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ስራ እንዲጀምሩ እና ያላቸውን አቅም እንዲያጎለብቱ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተጠቁሟል፡፡
ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እና ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን እንዲያመርቱም የሃይል እና የግብዓት ቅርቦትን ማሟላት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡