Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢልዋል ቡቶ ዛዲሪ ጋር በካራቺ ተወያዩ።

በውይይታቸው ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ለማሻሻል ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።

ግንኙነታቸው በተለያዩ የትብብር ማዕቀፎች እንዲጠናከሩ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው÷ በሁለትዮሽ ግንኙነት የተጀመረው ግንኙነታቸው ቀጠናዊ በሆኑ የጋራ ጉዳዮች እንደሚጠናከር ገልጸዋል፡፡

የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር ቢልዋል ቡቶ ዛዲሪ በበኩላቸው÷ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ በሁለቱ ሃገራት መንግስታት አበረታች ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካራቺ አዲስ የቀጥታ በረራ መጀመሩ ለግንኙኘታቸው እየተጠናከረ መምጣት ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ከአንድ አመት በፊት በኢዝላማባድ ኤምባሲዋን መክፈቷ በግንኙነታቸው አዲስ ምዕራፍ መክፈቱንም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛዲሪ አስታውሰዋል።

ወደ ፓኪስታን በማምራት የዲፕሎማሲያዊ ስራዎች እያከናወነ እና በቢዝነስ ጉባዔዎች ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በካራቺ የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ኢዝላማባድ ማምራቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.