Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ለመንግስት ሰራተኞች 45 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ለመንግስት ሰራተኞች 45 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡
 
ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የደመወዝ ጭማሪውን ያደረጉት በፈረንጆቹ የፊታችን ግንቦት 14 ቀን የሚካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
 
የደመወዝ ጭማሪው ዝቅተኛ ተከፋይ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ ወደ 15 ሺህ የቱርክ ሊሬ ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡
 
ቀጣዩን ምርጫ ቢያሸንፉም የተከሰተውን የዋጋ ንረት በመንግስት ሰራተኞች ላይ ጫና እንዳይፈጥር አስፈላጊ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡
 
ባለፉት 20 ዓመታት ቱርክን የመሩት ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በስልጣን ዘመናቸው በሀገሪቱ ታላላቅ ለውጦች ማስመዝገባቸውን አር ቲ በዘገባው አስፍሯል፡፡
 
በቱርክ ከፍተኛ ተጽዕኖ መፍጠር እንደቻሉ የሚነገርላቸው ኤርዶኻን የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም በቀጣዩ ምርጫ ይወዳደራሉ ተብሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.