ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከተለያዩ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከተለያዩ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ በብሪታኒያ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ጎን ለጎን ነው ከተለያዩ ሀገራት አቻወቻቸው ጋር የመከሩት፡፡
በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ ላይ እያደረገችው ያለውን ለውጥ እና ስራ አብራርተዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ አንደሆነ መናገራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡