Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሲካሄድ የነበረው ክልላዊ መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያፀደቃቸው የክልሉ መልሶ ግንባታ እቅዶችንና አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ ሲካሄድ የቆየው ክልላዊ መድረክ ተጠናቋል፡፡

መድረኩ በትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ ለማካሄድ ከክልል እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር የሚሰሩ እቅዶች ስትራቴጂዎችና አቅጣጫዎች ላይ የተሟላ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ታልሞ የተካሄደ ነው ተብሏል፡፡

በመድረኩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት፣ የወረዳና ከተሞች የስራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በዚሁ ወቅት አቶ ጌታቸው ረዳ÷ የትግራይ ክልልን መልሶ ግንባታ ለማረጋገጥ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ መሰረት በክልሉ ከላይኛው እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር ያለው አመራር በታያዙት ዕቅዶችና ስትራቴጂዎች ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም የትግራይ ክልልን ፖለቲካዊ ስነ ምህዳር የማስፋት ጉዳይ ለትግራይ ህዝብ የተሟላ ነጻነት ከማረጋገጥ ውጭ የሚያመጣው አሉታዊ ተጽእኖ እንደሌለም አብራርተዋል፡፡

በዚህም በዴሞክራሲ ያሉትን ግድፈቶች ማሟላትና ማስፋት፣ ፍትሐዊ አስተዳደርን ማረጋገጥ ይገባልም ነው ያሉት።

ህዝብ የማይፈልገውን አመራር ልናስቀጥል አንችልም ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው፥ በአስተዳደር ያለ ችግር በአስተማማኝ ደረጃ እስከተፈታ ድረስ ሊንቀሳቀስ የሚችል አቅም እንዳለና የፋይናንስ ችግርንም ማቃለል እንደሚቻል መግለጻቸውን የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.