Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወጣቱን ወደ ሥራ ለማስገባት በትኩረት እንደሚሰራ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወጣቱን ወደ ሥራ ለማስገባት፣ የፈጠራ ሥራዎችን እና ኢንቨስትመንትን ለማበረታት በትኩረት እንደሚሠራ አስታወቀ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን ከዘርፉ የክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር መክሯል፡፡

በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሀንስ አያሌው (ዶ/ር)፥ ባንኩ ተደራሽነቱን ለማስፋት ከሚሠራው ሰፊ ሥራ ባሻገር የሀገራችን ሥራ ፈጠራ ምህዳር ላይ ትልቅ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም 120 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ሥልጠና በመስጠት አብዛኞቹ ወደ ሥራ መግባታቸውን ነው የተናገሩት።

የኢንተርፕራይዞች የመስሪያና የመሸጫ ችግር ለማቃለልም ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ የሼድ ግንባታ እንደሚከናወንም ተገልጿል፡፡

ለዚህም ክልሎች የድርሻቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሀሳብ ፋይናንሲንግን ጨምሮ የሥራ ፈጠራና ሌሎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጀመሩ ሥራዎችን በቀጣይነት ይደግፋልም ነው ያሉት የባንኩ ፕሬዚዳንት።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.