Fana: At a Speed of Life!

ሕገ-ወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎችን በመቆጣጠር  ሃብቱን ለሀገር ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ማዋል ይገባል – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሕገ-ወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎችን በመቆጣጠር የወርቅ ምርትን ለሀገር ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ማዋል እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።

የማዕድን ልማት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የቀጣይ ሶስት ወራት ዕቅድ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጋምቤላ ከተማ ተወያይተዋል፡፡

በመድረኩ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ሺህ 275 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት ታቅዶ÷146 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም ወርቅ ብቻ ወደ ብሔራዊ ባንክ ማስገባት መቻሉ ተገልጿል፡

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ÷በክልሉ ሕገ ወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ቁጥር የጨመረው በአቋራጭ ለመክበርና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ለመፍጠር ከማሰብ ነው ብለዋል።

ሃብቱ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ግንባታ እንዲውል መንግሥት በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ የጀመረውን እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውንም  የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

የክልሉ ማዕድን ሃብት ልማት ዋና ዳይሬክተር አኳታ ቻም በበኩላቸው÷ በክልሉ በባህላዊና በዘመናዊ መንገድ የወርቅ ማዕድን እየተመረተ ቢሆንም ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የምርት መጠን መቀነሱን ጠቁመዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.