Fana: At a Speed of Life!

በኮቪድ 19 ስጋት አንዳንድ የጤና ተቋማት መደበኛ የህክምና አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ 19) ስጋት አንዳንድ የጤና ተቋማት መደበኛ የህክምና አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም ሳቢያ እናቶች በቤት ውስጥ እንዲወልዱ ሆኗል፤ በህክምና ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች የሰው ህይወት እያለፈ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ እንዳስታቀው መንግስት የኮቪድ 19 ህክምናን ብቻ የሚሰጡ ተቋማትን ስለለየ ሌሎች የህክምና ተቋማት መደበኛ የህክምና ስራቸውን ከዚህ ቀደሙ በበለጠ ማጠናከር እንዳለባቸው ገልጿል።

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት የህክምና ተቋሞቻቸውን የዘጉ እንዳሉም የገለፀው ሚኒስቴሩ፥ ተግባራቸው ትክክል እንዳልሆነ እና በፍጥነት ሁሉም ክፍት እንዲሆኑ አሳስቧል።

የተሟላ የህክምና አገልግሎት በማይሰጡት ላይ የህግ ተጠያቂነት እንደሚኖርም አስታውቋል።

ማህበረሰቡም ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተሳሰተ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ጤና ተቃማት እየሄደ እንደማይገኝ የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ ይህ ትክክል እንዳልሆነም አስገንዝቧል።።

በአሁኑ ወቅትም መደበኛ የህክምና አገልግሎቶች በአግባቡ እንዲሰጡ ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ ግብረ ሀይል ተቋቆሙ ወደ ስራ መገባቱንም አስታውቋል።

በተለይም የእናቶች እና ህፃናት ህክምና አገልግሎት፣ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች እና በወረርሺኝ መልክ የሚነሱ በሽታዎች ህክምና፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ህክምና
እንዲሁም የግል እና የአካባቢ ንጽህና የተለየ ትኩርት እንደሚሰጠው ገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር ለሁሉም የህክምና አገልግሎት እስከ 6 ወር የሚያቆይ የግብአት እጥረት እንደሌለበትም በመግለጫው ወቅት አስታውቋል።

በአልአዛር ታደለ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.