Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ እና አትላንታ ከተማዎች በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአትላንታ ከንቲባ አንድሬ ዲከንስና ከልዑካቸው ጋር ተወያይተዋል።

ከንቲባዎቹ በውይይታቸው÷ሁለቱ ከተሞች በጋራ በሚያከማውኗቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት መክረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ግንኙነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አትላንታ ቀጥታ በረራ መጀመሩን መነሻ በማድርግ የተጀመረ ነው ብለዋል።

በሁለቱ ከተሞች መካከል ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ግንኙነቶችን ለማጎልበት የሚያስችሉ ውይይቶችን ማድርጋቸውንም አንስተዋል፡፡

ይህም አዲስ አበባን የቱሪስት መዳረሻና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እድል የሚሰጥ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡

ከንቲባ አዳነች÷አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ከተሞችንና ተቋማትን መሳብ የጀመረችና በማበብ ላይ ያለች ታላቅ የዲፕሎማሲና የቢዝነስ ማዕከል መሆኗን አውስተዋል፡፡

ይህም የተሻሉ ልምዶችን መካፈል የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር በማድረግ ለከተማችን እድገት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.