Fana: At a Speed of Life!

ግብርናን የሚያዘምን የቴክኖሎጂ ውድድር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርናን ለማዘመንና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ወጣቶች ሀሳባቸውን የሚያወዳድሩበትና ወደተግባር የሚቀይሩበት ውድድር ተጀመረ።

ውድድሩ በሀገር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረግ ሲሆን፥ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን እስከ አስር የሚወጡት ደግሞ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ እንደሚመቻች የውድድሩ አዘጋጅ የሄይፈር ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ቴወድሮስ የሻወርቅ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የውድድሩ ተቀዳሚ ግብ ግብርናውን ማዘመን የሚችሉ ሀሳቦች ተግባር ላይ እንዲውሉ ማስቻል መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ውድድሩ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ግብርናው ላይ የሚሰሩ ተቋማት የሚሳተፉበት ነው።

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የአዳዲስ ስራ እድል ፈጠራ ዴስክ ሀላፊ ወይዘሮ አለምፀሀይ ደርሶልኝ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ የግብርውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለወጣቶች የመጣው እድል ግብርናውን ከማዘመን በተጨማሪ በርካታ የስራ እድል ይፈጥራል።

በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ የግብርና ቴክኖሎጂ ሀሳብ ያላቸው ከግንቦት 7 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

በታምሩ ከፈለኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.