Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ለተላለፈባቸው የ5 ሚሊየን ዶላር የፆታዊ ትንኮሳ ካሳ ይግባኝ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፈፅመዋል ለተባለው ፆታዊ ትንኮሳ ለተበየነባቸው የ5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ይግባኝ ጠየቁ፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ላይ የተላለፈው ብይን ከሁለት ቀናት በፊት ባሳለፍነው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ነው በኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት የተነበበው፡፡

የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን እንዲከፍሉ ብይን የተላለፈባቸው በፈረንጆቹ 1990ዎቹ አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ እና አምደኛ ኤሊዛቤት ጂን ካሮል ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ፈፅመዋል በሚል መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ሥም በአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዳልተነሳም ተመላክቷል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ÷ የተጠቀሰችውን ግለሰብ ከእነመፈጠሯም አላውቅም ሲሉ ሲ ኤን ኤን ባዘጋጀው መርሐ-ግብር ላይ በልጆቻቸው ሥም ጭምር ምለው ተናግረዋል ነው የተባለው፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በመርሐ-ግብሩ ላይ ከነበራቸው ቆይታ በኋላ በትናንትናው ዕለት ይግባኛቸውን በጠበቃቸው ጆ ታኮፒና ፊርማ ማንሃታን ለሚገኘው ፌዴራል ፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.