የሀገር ውስጥ ዜና

ኤጀንሲው ከ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

By Alemayehu Geremew

May 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃና አገልግሎት ኤጀንሲ 2 ቢሊየን 847 ሚሊየን በላይ ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

የኤጀንሲው ዳይሬክተር ሀሰን ሞሳ እንዳስታወቁት ÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ነው 2 ቢሊየን 847 ሚሊየን 951 ሺህ 691 ብር የተሰበሰበው፡፡

ገቢው 105 ሺህ 612 ለሚሆኑ ተገልጋዮች ልዩ ልዩ አገልግሎቶች በመስጠት የተሰበሰበ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል፡፡

ተቋሙ ለዚህ ስኬት የበቃው የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ሁሉንም ተገልጋዮች በአጭር ጊዜና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ማስተናገድ በመቻሉ እንደሆነ መናገራቸውንም ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡