Fana: At a Speed of Life!

የወረዳ ስራ አስፈፃሚውን የገደለው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዋለ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ከግል ጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳ ስራ አስፈፃሚውን የገደለ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በፖሊስ አባል መገደላቸው ታውቋል፡፡

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽህፈት ቤት ማመልከቱ ተገልጿል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም “ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ” በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ መግደሉ ታውቋል፡፡

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የፖሊስ አባሉ በፈፀመው ድርጊት ማዘኑን ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.