የሀገር ውስጥ ዜና

የአትላንታ ከንቲባ “ክሪኤቲቭ ሃብ ኢትዮጵያ” የተሰኘውን ማዕከል ጎበኙ

By Alemayehu Geremew

May 12, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲከንስ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ“ክሪኤቲቭ ሃብ ኢትዮጵያ” ማዕከልን ጎበኙ፡፡

በከንቲባው የተመራው የልዑካን ቡድን በማዕከሉ በመገኘት በወጣት ሥራ ፈጣሪዎችና የፈጠራ ባለቤቶች የተሰሩ የፈጠራ ውጤቶችን መጎብኘታቸውንም የኢንተርፕራይዙ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከንቲባ አንድሬ ዲከንስ በኢትዮጵያ ለስራ ፈጣሪዎች ምቹ ዕድሎች መኖራቸውን ጠቅሰው፥ የፈጠራ ሐሳቦች ወደ ገንዘብ እንዲለወጡ በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

“ክሪኤትቭ ሃብ ኢትዮጵያ” አዳዲስ ሐሳብ ያላቸው ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ሐሳባቸውን ወደ ተግባር መለወጥ እንዲችሉ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ የሚገኝ ማዕከል ነው።