ቴክ

ኤሎን መስክ ለትዊተር አዲስ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሾሙ

By Alemayehu Geremew

May 12, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤሎን መስክ ሊንዳ ያካሪኖን አዲሷ የትዊተር ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡

የጣሊያን የዘር ሐረግ ያላቸው የ63 ዓመቷ ሊንዳ ያካሪኖ ÷ በትዊተር ኩባንያ ውስጥ በዋናነት በንግድ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሠሩ ኤሎን መስክ አስታውቀዋል።

እርሳቸው ደግሞ በምርት ዲዛይን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማዳበር ላይ እንደሚያተኩሩ አመላክተዋል፡፡

የቀድሞው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አያይዘውም በኩባንያው ውስጥ የሚኖራቸው ሚና ዋና የቴክኖሎጂ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል።