የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀን ክብረ በዓልን አስመልክቶ ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀን ክብረ በዓልን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ለተወሰነ ሰዓት መንገድ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።፡
“የሚጠብቁን ጀግኖችን እናክብር” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ24ኛ በሐገራችን ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ የሚከበረውን የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ዝግ ይደረጋሉ።
በዚህ መሰረት
ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ እና ከላንቻ ወደ መስቀል አደባባይ አራተኛ ክፍለ ጦር ዝግ የሚደረግ ሲሆን ለከባድ ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ ይሆናል።
ከከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ ለገሐር መብራት፣ ከጎማ ቁጠባ በብሔራዊ ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ መስቀለኛ ወይም ክቡ ባንክ፣ ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል መስቀለኛ፣ ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ መንገዶች ከማለዳው 12:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ ረፋዱ 5:00 ሠዓት ድረስ መንገዶቹ ዝግ የሚሆኑ ሲሆን አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡