Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት የኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው የለም

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ የኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው አለመኖሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

24 ሰአታት ውስጥ ለ965 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በ24 ሰአታት ውስጥ በተደረገው ምርመራም ቫይረሱ የተገኘበት ሰው አለመኖሩንም አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 116 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 90 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ፤ 21 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ይታወቃል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.