የግብርና እና ሳይንስ አውደ-ርዕዩ ለግብርናው ዘርፍ ፈጣን እድገት የሚያግዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡበት ነው – ተሳታፊዎች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና እና ሳይንስ አውደ-ርዕዩ ለግብርናው ዘርፍ ፈጣን እድገት የሚያግዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡበት መሆኑን የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ገለጹ።
የግብርና ሚኒስቴር፣ የግብርና ትራስፎርሜሽን ኢንስቲትዩትና ኢትዮ-ቴሌኮም “ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ሃሳብ በጋራ ያዘጋጁት የግብርና እና ሳይንስ አውደ-ርዕይ በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።
በአውደ-ርዕዩ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ዘመናዊ የሆኑ ወጪና ጊዜ ቆጣቢ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል።
ከአውደ-ርዕዩ ተሳታፊዎች መካከል ከሬንሲስ ኢንጂነሪግ ድርጅት ለሚ አሰፋ÷በፀሐይ ኃይል ውሃ መሳብ የሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለዕይታ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
የቴክኖሎጂ ውጤቱ በተለይም በገጠር አርሶ አደሮች የፀሐይ ብርሃን ተጠቅመው በቀላሉ ውሃ ለመሳብ የሚያስችላቸው መሆኑን አብራርተዋል።
በግብርና ሚኒስቴር በኩልም የተቀናጀ የዓሳ እርባታ ዘዴን ማከናወን የሚያስችል ቴክኖሎጂ ለዕይታ ቀርቧል።
በሚኒስቴሩ የዓሳ ሃብት ባለሙያዋ አቻም የለሽ ቱሬሳ÷ ዓሳን፣ ዶሮንና አትክልትን በአንድ አነስተኛ ሥፍራ ማምረት የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት።
የቆላ ዝንብ ማራባትና ማምከን ፕሮጀክት የኤስ አይ ቲ ዴስክ ኃላፊ ሞገስ ሂዶቶ በበኩላቸው÷ በቴክኖሎጂ በታገዘ የላቦራቶሪ ምርምር የቆላ ዝንብን ለማጥፋት የሚያስችል ቤተ-ሙከራ በአዲስ አበባ መቋቋሙን ገልጸዋል።
የተቋቋመው ቤተ-ሙከራም ከኢትዮጵያ አልፎ ለ38 የአፍሪካ አገራት ጥቅም እየሰጠ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አዳዲስ የእንስሳት ዝር