Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ በሚዛን አማን የሌማት ትሩፋትና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በሚዛን አማን ከተማ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ዝግጅትና የሌማት ትሩፋቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በወጣቶች የተዘጋጁት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የአቮካዶና የፓፓዬ ችግኞች ለተከላ ብቁ መሆናቸውን ተመልክተዋል።

በቅርቡ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ስራ አካል የሆኑት የዓሳ ኩሬና የወተት ላሞች እርባታ ያሉበትን ደረጃ አቶ አደም ፋራህ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንም የፖርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር (ኢ/ር)፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ ጸጋዬ ማሞ እንዲሁም የክልሉና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.