የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የአምራቾች አውደ ርዕይ ተከፈተ

By Tamrat Bishaw

May 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ለ8ኛ ጊዜ የተዘጋጀ የአምራቾች አውደ ርዕይ በደብረብርሃን ከተማ ተከፍቷል፡፡

አውደ ርዕዩ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በይፋ መከፈቱ ተገልጿል፡፡

በክልሉ የሚገኙ የሁሉም ኮሌጆች አሰልጣኞች ፣ሰልጣኞችና ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ ሆነዋል።

የክልሉ ስራና ስልጠና ቢሮ ሀላፊ አቶ አረጋ ከበደ የዐውደ ርዕዩ ዓላማም ፈጠራንና ክህሎትን ይበልጥ ለማሳደግ እና የገበያ አማራጮችን ለማፈላለግ ነው ብለዋል።

ምርቶቻቸውን ለእይታ ያቀረቡ አምራቾች በሰጡት አስተያየት አውደ ርዕዩ ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚረዳቸው እና የገበያ ትስስር እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል።

በክልል ደረጃ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ለአራት ቀን የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።

ተሳታፊዎቹ ክልላዊ አውደ ርዕዩን ካጠናቀቁ በኋላ በፌደራል ደረጃ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው ዝግጅት ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።

በአላዩ ገረመው