Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር  ከዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 15፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ ከዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አዴል ኮድር ጋር በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡

በውይይታቸውም   ያለ እድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለመከላከልና ለማጥፋት በተዘጋጀው ሀገራዊ ፍኖተ ካርታ አተገባበር  ላይ  ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

በዚህም የፍኖተ ካርታውን ትግበራ በተወሰኑ እና ችግሩ ጎልቶ በሚታይባው ቦታዎች ላይ በመጀመር ወደ ሌሎች አካባቢዎችን ማስፋት እንደሚገባ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ነው የተባለው።

ከዚያም ባለፈ  ትግበራው የሁሉንም ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች በማስተባበር መከናወን እንደሚገባው ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ነው የተነገረው።

በሌላም በኩል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ10 ዓመት ስትራቲጂክ እቅድ ዝግጅትና ትግበራ ላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ተሳትፎና ግብዓት ወሳኝ በመሆኑ የሁሉንም ሀሳብና ግብዓት እንዲሁም ድጋፍ ማግኘት  እንደሚገባም   ተጠቁሟል፡፡

ከኮቪድ- 19 ጋር በተያያዘም በተለይም ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ ህፃናት እና ከስደት ተመላሽ ህፃናት ከሚያስፈልጓቸውን ድጋፎች መካከል የስነልቡናና ማህበራዊ ድጋፍ አንዱ እና ወሳኝ  ጉዳይ ነው ተብሏል።

በመሆኑም  በሀገሪቱ በሚደረገው የመከላከል ጥረት ውስጥ የሶሻል ወርክ ባለሙያዎችያላቸው ሚና  ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸውን የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.