የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከዓለም ባንክና ገንዘብ ሚኒስቴር ተወካዮች ጋር እየተወያየ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከዓለም ባንክና ከገንዘብ ሚኒስቴር ተወካዮች ጋር እየመከረ ነው፡፡
በመድረኩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰውን ጨምሮ የዓለም ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ተወካዮች እንዲሁም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ አባላት ተገኝተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ በትግራይ ክልል በነበረው ግጭት ውድመት የደረሰባቸውን ተቋማትን መልሶ መገንባትና ማቋቋም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
በክልሉ በነበረው ግጭት የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ በቀረበው የዳሰሳ ጥናት ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑንም ከጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡