Fana: At a Speed of Life!

የምርት አቅርቦትን በማሳደግና የዋጋ ግሽበትን በመቀነስ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራል – አቶ አብዱጀባር መሃመድ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የምርት አቅርቦት በማሳደግና የዋጋ ግሽበትን በመቀነስ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱጀባር መሃመድ ገለጹ፡፡

በሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በክልሉ ከሚገኙ ከሁሉም ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ አቶ አብዱጀባር መሃመድ እንዳሉት÷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተለዋዋጭ በሆነ ቀውስ እና በሌሎች አያሌ ምክንያቶች የሸቀጦች ዋጋ ንረት በመከሰቱ በነዋሪዎች ላይ ጫና አሳድሯል ።

ሕዝቡን ለምሬት እየዳረገ የሚገኘው የኑሮ ውድነት ችግርን ለመቋቋም የሀገር ውስጥ ምርት ማሳደግን አብይ ጉዳይ በማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚስተዋለውን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ መቆጣጠር እንዲሁም ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች የስራ እድል ማመቻቸት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

መንግስት የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል በሁሉም መስክ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑንም ሃላፊው ጠቅሰዋል።

ጽንፈኝነትና አክራሪነት አስተሳሰቦችን በመታገል የሀገሪቱን አንድነትና ሰላም ማስጠበቅ እንደሚገባ መግለጻቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.