Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትግራይ ክልል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ግምታቸው ከ5 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ የሆኑ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ ኮምፒውተሮችን ጨምሮ የተለያዩ የት የምህርት ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ገላና ወልደሚካኤል (ዶ/ር) በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት÷ የትግራይ ክልል ተማሪዎች ላለፋት ሦስት ዓመታት ከትምህርት ገበታ ርቀው ቆይተዋል፡፡

አሁን ባለው የሠላም ስምምነትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተመልሰው ማየት እንፈልጋለን ነው ያሉት።

የተደረገው ድጋፍም ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝ መሆኑን ገልፀዋል።

ከትግራይ ክልል የሐብትና የትምህርት መሣሪያዎች አሰባሳቢ ኮማቴ ሰብሳቢ ተሥፋዬ አረጋዊ በበኩላቸው ÷ በጦርነቱ ትምህርት ቤቶችና የትምህርት መሠረተ ልማቶች መውደማቸውን ገልጸው÷ ለተደረገው ድጋፍ አመሥግነዋል።

በቀጣይ ሌሎች አካላትም ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ ህፃናትን ወደ ትምህርት የመመለስ ሥራውን እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.