Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለሰላም ሥምምነቱ ትግበራ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ናት – ሞሊ ፊ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት ትግበራ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ተናገሩ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም በሁለትዮሽ እና የጋራ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በውይይቱ አቶ ደመቀ ለረዳት ሚኒስትሯ ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት አተገባበር ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ረዳት ሚኒስትሯም የሰላም ስምምነቱን አድንቀው ሀገራቸው ለአተገባበሩ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

በቀጠናዊ ጉዳዮች በተለይም ሱዳንን በተመለከተ ባደረጉት ውይይትም የሱዳን የሰላም ሂደት በሱዳናውያን ባለቤትነት መካሄድ እንዳለበትና ጎን ለጎንም ችግሩን የሚያባብሱ ጉዳዮችን ለመቅረፍ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.