የሀገር ውስጥ ዜና

የአርሶ አደሮችን  የውሃ ችግር ለመቅረፍ የዝናብ ውሃን በአግባቡ መጠቀም ይገባል – አቶ ሙስጠፌ

By Mikias Ayele

May 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሶ እና አርብቶ አደሮች የሚያጋጥማቸውን የውሃ ችግር ለመቅረፍ ከዝናብ የሚገኘውን ውሃ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በቆራሄይ ዞን ላስደንከይሬ ወረዳ የሰርዳሌ መካከለኛ መስኖ ልማትና የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን መርቀው ከፍተዋል።

አቶ ሙስጠፌ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ የውሃ ፕሮጀክቶች በክልሉ ቆላማ አከባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮችን ሕይወት ያቃልላሉ፡፡

ሰሞኑን በክልሉ ጀረር፣ቆራሃይና ሸቤሌ ዞኖች በጉብኝት ላይ የሚገኙ ት አቶ ሙስጠፌ በሸቤሌ ዞን የኤሌሌ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን መርቀው መክፈታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን  መረጃ ያመላክታል፡፡