Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት “ይሻሻል ፤ አይሻሻል ” በሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሕገ መንግስቱ ይሻሻል እና መሻሻል የለበትም” በሚሉ አከራካሪ ጉዳዮች ዙሪያ በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ውይይት ተካሂዷል፡፡

“ሕገመንግስቱ ከሦስት ዓስርት ዓመታት በኃላ ሊሻሻል ይገባል ወይ? ከሆነስ ምን ምን ላይ ይሻሻል?” በሚል ርዕስ የተካሄደ የጥናት ግኝት ለባለድርሻ አካላት ቀርቧል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ ሕገ መንግስቱ ብዙ አከራካሪና አሻሚ ጉዳዮች ያሉት በመሆኑ ከውይይቱ አራሚና አስታራቂ ሃሳቦች ይገኙበታል ተብሎ ይታመናል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ሀገራዊ ችግሮች በሳይንሳዊ ጥናት መፍትሄ እንዲያገኙ ነው እየሰራ ያለው ሲሉም ተቋሙ ከተቋቋመ ጀምሮ ያበረከተውን ጉልህ ድርሻ አስታውሰዋል።

የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት ÷ከሕገመንግስቱ በጭራሽ መሻሻል የለበትም ፤ ህገ መንግስቱ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ መተካት አለበት እና ጥናትን በተከተለና በአካታች ውይይት ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል የሚሉ ዋና ዋና እሳቤዎች እንዳሉ የጥናቱ ግኝት አመላክቷል፡፡

ህገ መንግስቱ መሻሻል የለበትም እና ሙሉ በሙሉ መጣል አለበት የሚሉት ከሕገ መንግስት አንፃር ተቀባይነት የላቸውም ያሉት ሚኒስትር ፥ ዴዔታው በአካታች ውይይት መሻሻል አለበት የሚለው እሳቤ ግን ተመራጭና ተቀባይነት ይኖረዋል ነው ያሉት።

በማርታ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.