አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሁለቱ አካላት በቆይታቸው ኢትዮጵያና አሜሪካ በሁለትዮሽ ፣ ቀጠናዊ እና በባለብዙ ወገን ያላቸውን ትብብር ማጠናከርበሚያስችላቸውጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
አምባሳደር ጃኮብሶን በሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ አሜሪካ ዜጎቿን ለማስወጣት ባደረገችው ጥረት ላይ ኢትዮጵያ ላሳየችው ትብብር ምሥጋና ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡