Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ፡፡

በዛሬው እለት 9 ሰዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የፋሲል ከነማ የማሸነፊያ ግቦችን የአማካይ ተጫዋቹ ሱራፌል ዳኛቸው በ45ኛው እና በ94ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ምሽት 12 ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ መድን ድሬደዋ ከተማን 3 ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በዚኅም የአማካይ ተጫዋቹ ወገኔ ገዛኸኝ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር የአጥቂ መስመር ተሰላፊው ብሩክ ሙሉጌታ አንዷን ጎል አስቆጥሯል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.