ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ

By Shambel Mihret

May 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ፡፡

በዛሬው እለት 9 ሰዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የፋሲል ከነማ የማሸነፊያ ግቦችን የአማካይ ተጫዋቹ ሱራፌል ዳኛቸው በ45ኛው እና በ94ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡